ለፊደል
እና ለትውፊት የሬድዮ ፕሮግራም የተገዙት መቅረፀ ድምፆች የውሀ ሽታ ሆነዋል
ለፊደልና ለትውፊት የሚያገለግል ኋላ ቀር መቅረፀ ድምፅ |
የፊደል
እና የትውፊት የሬድዮ ፕሮግራም በድምሩ የሁለት ሰአት የአየር ሽፋን የያዘ ሲሆን በሶስት መቅረፀ ድምፆች ብቻ ሲሰራ ቆይቷል።
መቀሌ
ዩንቨርስቲ ለዚህ በጀት መድቦ ተጨማሪ መቅረፀ ድምፆች እንደተገዙ ከተነገረ ሰንበትበት ያለ ሲሆን እስካሁን ድረስ ግን የመቅረፀ
ድምፆቹ ወሬ የውሀ ሽታ ሆኖ ሰንብቷል።
የመቀሌ ዩንቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ትምህርት ክፍል ዲን የሆነው መምህር መብርሀቴን ይህን
ችግር በተደጋጋሚ ለበላይ አካላት አሳውቆ ምንም አይነት መፍትሄ እስካሁን እንዳልተገኘ እና ከዛሬ ከነገ መቅረፀ ድምፆቹ እጃችን
ይገባሉ በሚል ያልትጭብጠ የስፋ እየተጓዙ እንደሆነ ተናግሯል።
በማከልም “እስከ አርብ ግንቦት 21 2007 ዓ.ም አምስት መቅረፀ
ድምፆች ይደርሱናል” ሲል የተለመደ የተስፋ ቃሉን አስቀምጧል። የመቀሌ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንትም ዶክተር ክንደያ ገ/ህይወትም በበኩላቸው
“ይህ በማንኛውም የስራ ዘርፍ ሊያጋጥም የሚችል ችግር ስለሆነ ተማሪው በትእግስት ሊሰራ ይገባል። መቅረፀ ድምፆች ተገስተዋል። በቅርቡ
እጃችው ይገባሉ” ሲሉ ያላቸውን እስተያየት ገልፀዋል።
No comments:
Post a Comment