ፊደል
የሬድዮ ፕሮግራም ለሁለተኛ ሳምንት ተስተጓጎለ
በናሆም ታደሰ
በእየሳምንቱ
ቅዳሜ ከ ስድስት ሰአት እስከ ሰባት ተኩል በመቀሌ ዩንቨርስቲ በጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል እና በድምፂ ወያኔ ትብብር
የሚቀርበው ፊደል የሬድዮ ፕሮግራም ለሁለተኛ ሳምንት ተስተጓጎለ።
በተማሪዎች እየተዘጋጀ የሚቀርበው ይህ ፕሮግራም በመብራት መጥፋት
ምክንያት ግንቦት 1 2007 ዓ.ም የተላለፈው ፕሮግራም የይድረስ ይድረስ በመዘጋጀቱ ምክንያት አጥጋቢ ባልሆነ ኤዲቲንግ መቅረቡ
ይታወሳል። ይህ ችግር ለሚመለከተው አካል ተነግሮ የተቀረፈ ቢሆንም ግዜአዊ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ባለመገኘቱ በተለምዶ ህዳሴ ህንፃ
በመባል የሚታወቀው ኤዲት
የሚደረግበት ህንፃ በድጋሚ ተበላሽቷል።
በመሆኑም የግንቦት 7 2007 ዓ.ም ፕሮግራም በድጋሚ የይድረስ
ይድረስ በመሰራቱ ተመሳሳይ እጣ ገጥሞታል። የኤዲቶሪያል ኮሚቴ አባላት በችግሩ በጣም እንደተማረሩ እና ትምህርታቸው ላይ ተፅእኖ
እያሳደረ እንደሆነ በግልፅ አስቀምጠዋል።
ችግሩ በአፋጣኝ ዘላቂ ምላሽ ካልተሰጠው ፕሮግራሙ እንዲሁ እንደተስተጓጎለ የሚቀጥል መሆኑሠንም
አክለው ተናግረዋል።
![]() |
ፊደል ሬድዮ ፕሮግራም ሲስተጓጎል |
No comments:
Post a Comment