ደም
በመለገስ የአዲስ አበባ ክብረ ወሰን በመቀሌ ተሻሻለ
በናሆም ታደሰ
![]() |
በአይደር ሆስፒታል ደም በመለገስ ላይ የሚገኝ አንድ ተማሪ |
ባሳለፍነው
እሮብ ሚያዚያ 21 2007 ዓ.ም በመቀሌ ዩንቨርስቲ በአራቱመ ግቢ የተካሄደ የደም ልገሳ ነበር።
ከሁሉም ግቢ የተውጣቱ ተማሪዎች
በአይደር ግቢ በመገኘት ደም የለገሱበት ምክንያት በአዲስ አበባ ተይዞ የነበረውን የበጎ ፈቃደኝነት የደም ልገሳ ክብረ ወሰን ለማሻሻል
እንደነበረ ታውቋል።
ክብረ ወሰኑን ማሻሻለ ከመቻሉም አልፎ ከሶስት አመት በፊት በአጠቃላይ በመቀሌ የነበረው የበጎ ፈቃደኝነት የደም
ልገሳ 18 በመቶ እንደነበረ ይታወቃል። በአሁኑ ወቅት ይህ ቁጥር 83 በቶ ከመድረሱም ባሻገር ከ60 እስከ 65 በመቶ የሸፈነው የዩንቨርስቲ
ተማሪ ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አስተባባሪው ተማተሪዎች በዩንቨርስቲ ቆይታቸው እንደዚህ አይነት መልካም ምግባሮችን በመከወን ሰብአዊነት
የሞላወ ድርጊትና የህሊና እርካታን መኛግኘት ይችላሉ ሲል መልክቱን አስተላልፏል።
ደም ሲለግሱ ያገኘሁዋቸው ተማተሪዎችም ደም በመለገሳቸው
የተማሪዎችን እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ህይወት መታደግ በመቻላቸው ደስታ እንደተሰማቸውና ይሄን እድል ላላገኙ ሁሉ የድረሱ
ጥሪ በማስተላለፍ ስሜታቸውን ለመግለፅ ሞክረዋለ።
No comments:
Post a Comment