Wednesday, August 26, 2015



ማዶ ለማዶ

እዚህ ማዶ አንድ ጎመን እዚያ ማዶ አንድ ጎመን
የእኛማ ጋሽዬ ሊሄዱ ነው ጀርመን::
እዚህ ማዶ… እዞያ ማዶ…
እዚና እዛ ማዶ በርቀት ዘምሮ
ቁራሽ  ስንዴ ጉርሻ ጣሳ ጠላ ማትሮ
በዝማሬው ሳይቀር በግጥሞቹ ቃላት አጥናፍ የሰነገን
በምን ያቀርቡታል ተራርቆ ያደገን?
የለመዳት እፍኝ ከእማምዬ ጓዳ ተጋግራ እንድትቆየው
ቅርበት አይዘምርም ርቀት ነው ሚታየው::
ፊት የሚጠብቀው ቁራሽ ፍርፋሪ
ከጎኑ ዞር ቢል ሆ ሚል አጫፋሪ
ታድያ አጅሬ ይሄኔ
እዚህ ማዶ ብሎ እዚው አይጨርስም እዛ ማዶ ይሄዳል
አድጎ ገንጥሉኝ ቢል በማን ይፈረዳል?

ናሆም ታደሰ
የልጅነት ተፅእኖ በጉልምስና አሻራ አለው

ምስለ ማሲንቆ

አወይ ማሲንቆዬ…
በፈረሱ ጭራ ለስልሳ የተቃኘች
ከላይ ስነካካት ከስር ገዝግዝ አለች።
እኔ መቼ ገባኝ
ለካ የሲቃው ባቲ ጣፋጭ የሚሆነው
ከስርም እንደላይ ሲገዘግዙት ነው።
ካንቺ ባቆራኘኝ የሙዚቃ ዘመን
እኔ እያለው በይወት ከሌላ ገዝጋዥ እጅ ወድቀሽ ያየሁሽ ቀን
በመገዝገዣዬ ደካማነት ባምንም
ሙዚቀኛሽ እኔ ራስ ወዳድ አልሆንም።
በስልቱ የተካነ በዜማው ከጠራሽ
የሌላ አዝማሪ ግዝገዛ ከረታሽ
እኔ ራሴ ወስጄ ልስጥሽ ለዛ አዝማሪ
በጣቶቹ ርኪ በግዝገዛው ኑሪ
ሂጂ ማሲንቆዬ ለፈረስሽ ጭራ
የሚመጥን ገዝጋዥ ወዳለበት ስፍራ።
ምክንያቱም ትዝታሽ ጣፋጭ የሚሆነው
አምባሰል አንቺሆዬሽ ግሩም የሚሆነው
ከስርም እንደላይ ሲገዘግዙሽ ነው።


ናሆም ታደሰ
100# 50 እና 10 ብር
የቸገረኝ ቀን ነው የተራብኩኝ ሰዓት
100# 50 እና 10 ብር የሰጡኝ አባት
ይህ መቶ ብር ማለት አባወራው ገንዘብ
ዝግጁ ነውና ሲርብህ ለማጥገብ
ለኦና ጎተራህ ለራበው ስልቻህ መፍትሄ ስላለው
የብር አረንጓዴን ልምላሜ በለው::
ደሞ እንካ 50 ብርን ቀለሟ ቢጫ ነች
መቶ ጋ ለመድረስ ተስፋ ትሆንሀለች::
ስለዚህ ቢጫዋን ተስፋ ብለህ ጥራት
ካባወራው ስፍራ የሚጥል መሰላል ስለምታይባት::
50ን በዚህ እናብቃ
መቼም ሠው አይኖርም በተስፋ ዘላለም
ከስር የምታያት ይቺ ቀይ ቀለም
አንድ የጎዳና ልጅ ርሀብ የፀናበት
እንደሰማይ ኮከብ ተስፋው የራቀበት
ሺ ግዜ ቢናጥጥ ኪሱ ምታገኘው
ስንት መስዋት ሆኖ የመነተፋትን ይቺን 10 ብር ነው::
ከተፈተነባት በለጋነት ወራት በጨቅላነት እድሜ
አውጣላት ላስር ብር ደም የሚል ስያሜ::
አረንጓዴ# ቢጫ# ቀይ
ልምላሜ# ተስፋ እና ደም
ከዚህ በላይ ትርጉም ከዚህ በላይ ፍቺ የትም ሀገር የለም::

ናሆም ታደሰ


(የሰው ልጆችን ባህሪና እጣ ከሚናገሩት የወራት ኮከቦች በግንቦት ወር በተወለደ ሰው ኮከብ ላይ የተመሰረተ ግጥም)
ኮከብሽ ሲፈታ
ግንቦት ነው ውልደትሽ በግለቱ ፀሀይ
ሀሩር ሲገባደድ ለዝናብ ሩብ ጉዳይ::
እና በዚህ ወር ላይ ወደምድር የመጣ
ውዝግብግብ ነው እድሉ አከራካሪ እጣ
ግትር ነው ልቦናው ጨካኝ በባህሪ
እማ እንዲ ነሽ እንዴ ለሰውም አትራሪ?
ደሞ ዝቅ ብሎ ኮከብሽ ሲነበብ
ግሩም አይምሮ አለው የሰላ አስተሳሰብ::
ይህን ማን ይክዳል?
እጅሽ ካላጠረ የሙት ልጅ ካበላ
ከወዴት ሊመጣ ካንቺ በላይ የሰላ?
በፈጠረሽ እማ
ይህን ስል አይምሮ የአብራክሽ ክፋይ ለምነው ያልወረሰው?
ወይ አንቺ ራስ ወዳድ ወይም ደሞ ልጅሽ ማሰብ ያቃታው ነው ::
ትዝ ይልሻል እማ በሳት ዳር ጨዋታ
የእግሮችሽን ቅጥነት የጠየኩሽ ለታ?
አንቺማ ዋሸሺኝ እንዳይቀንስ ፍቅሬ
የእሳት ልጅ እሳት ነው ደረስኩበት ዛሬ::
እጣ ክፍሉ ሆኖ ግንቦት የወለደው
ቤት መዋል ይጠላል እግረኛ ተጓዥ ነው::
መጓዝ አይጠላም መገስገስ ደግ ነው
ግን እማ ያንቺን ጉዞ ዳና ስ ያረገው
ወደላይ ነው እንዴ ልቴጅ የፈጠረሽ?
የመሬት ስበት ነው እዚያው የመለሰሽ?
አንቺ ብትሸሽጊኝ ሀቅኮ ንጋት ናት አትቀር ተደብቃ
ጉደኛ ኮከብሽ መች በዚህ ሊያበቃ…
በዚህ ወር ዓለምን የተቀላቀለ
ብዙ ልጅ የለውም የሚል ሀረግ አለ::
እዚ ላይ እውነት አለው ካላደለሽ ባርኮ
ካብራክ የወጣ ሁሉ ልጅ አይደለምኮ::
ስል ካማጠ ሆድሽ መጋዝ ከፀነሰ
ባቢሎን ካረገዝሽ ሳይቋጭ የፈረሰ
ማህፀንሽ ከከዳ ጭድ ከበቀለበት
መወለድ ቋንቋ ነው ፊደል ነው ልጅነት::
እማኮ ትንፋሽሽ
ቁርጥ ቁርጥ ይላል ብዬ ስጠይቅሽ
ደበቅሽኝ ደዌሽን አልችል አለ አንጀትሽ::
እውነቱ ግን እማ…
የዚህ ወር ዘለላ ገና ከጥንስሱ
ትንሽ ደከም ይላል አተነፋፈሱ::
ሳንባሽም ደከመ? እና ምን ቀርቶሻል?
ትንባሆ ገሎሻል ወይ ድመት ወልደሻል
ምንድነው የደበቅሽኝ? እስትንፋስ ቀልድ ነው?
አዳምኮ ያኔ ህይወቱን የዘራው በጌታ ትንፋሽ ነው::
ደሞ ዝቅ ስንል ኮከብሽ እንዲ ይላል
ግንቦት የሚወለድ ጆሮውንና አንገቱን ብዙ ግዜ ያመዋል::
እዚህ ላይ ፉርሽ ነው ቀባጣሪ ኮከብ!
ለሀዘን ፅዋ አርጎሽ ለመከፋት ሰበብ
አንድ ለናቱ ሆነሽ በጤነኞች መሀል
ምን የቀረሽ አለ ያልታመምሽው አካል?
ቆይ እንጂ ረጋ በይ ስሚ ኮከብሽን
ሩቅ ማሰብ ሩቅ ማለም ቶጃለሽ ያለሽን
በዚ እንኳ አትታሚም አንደራደርም
ያንቺን የሩብ ግማሽ ዘንዶም አያልምም::
ግን እማ ንገሪኝ
ሲመሽ አስተዳድሮሽ ሲነጋ ሚከንፈው
የተካነ ጠበብት ሎሬት የማይፅፈው
ብርሀን የሚፈራው ያ ጭሱ ራእይሽ
ለምፃት ነው እንዴ የሚፈታው ህልምሽ?
ጉዱን ለቀባሪው ማርዳት ባይሆንብኝ
ልንገርሽማ እማ ምን እንዳነበብኩኝ
ካስራ ሁለት ወር ነጥቆ ግንቦት የወለደው
ስነ-ፅሁፍ ወዳድ ጥበብ አድናቂ ነው::
ይሄማ ግልፅ ነው ጥበብሽ መች ታጣ
ድሮ አንቺ የሌለሽን 'ኔ ከየት ላመጣ?
ግን እማ እኔ ያልገባኝ…
መቶ ሀያሲ ታቅፎ ሺ ሎሬት ደርድሮ
ከእልፍኝ በማይወጣ በጭብጨባ ታስሮ
የግዜ እርከን መሆን የጠቢብ ጣራ ነው?
ምን ካንቺ ባላውቅም ጥበብ ማለትኮ ሀገር ሲቀይር ነው::
ግርምቴን ልቀጥል? እማ አታዝኚብኝም?
ብርቅኮ ሆኖብኝ ነው! ጉደኛ ኮከቤ ምን አለ አትይኝም?
የዚህ ወር አርበኛ ከሌላ ሚለየው
ባካልም ባይምሮም የተዋበ ሰው ነው::
ይገርማል አይደለ? ይህን እንኳ አታቂም
ውበት በባህሪው ለተመልካች እንጂ ለራስኮ አይታይም::
ለምን ይመስልሻል ያ ሁሉ ተጋዳይ
ጦር ጎራዴ ይዞ የመጣው ባንቺ ላይ?
ጀግና የተጣላብሽ ቆንጆ ነሽ እመኚኝ
ይልቅ እሱን ትተሽ ምን ገረመህ በይኝ
እንዴት የተዋበ አስቀያሚ ይወልዳል?
ከተሳለ አይምሮስ ጭፍጋግ አስተሳሰብ እንዴት ይፈጠራል?
ምን ዥንጉርጉር ቢሆን ሺ ቢያደላ የእናት ሆድ
ተባርኮ ፀንሶ ያለም መርገም ይውለድ?
አዎ አንቺማ ሳቂ…ደሀውን ይግረመኝ
ወዳጄ ኮከብሽ ጠንካራ ፍላጎት እንዳለሽ ነገረኝ::
አሁን እኔ ልሳቅ…
እማ አሁን ፍላጎት ምን ያደርግልሻል?
ምሰሶ ያላርማታ ብቻውን ሲፀና የት ሀገር አይተሻል?
ለፍላጎትማ አዳምስ ሲፈጠር
የጌታውን ወንበር ተመኝቶ አልነበር?
እስኪ ብቻ ተይው…
ይህ ሁሉ በባህሪሽ የባህር ውሀ ነው ቢቀዝፉት አይደርቅም
እንኳን በኔ አንደበት በራስሽ አያልቅም::
እንዲ እንዳስገረምኩሽ አልቀርም አትስጊ ብዙ አወጋሻለው
ደሞ ሌላ ጊዜ የልጅሽን ኮከብ የኔን ነግርሻለው::

 ናሆም ታደሰ



Wednesday, July 22, 2015

የኔ ቢጤ
አምስት አስር ሳንቲም ስለምን ያየኝ ሠው
ያገሬው ከበርቴ ዝና የተላበሰው
እራሱን አዋርዶ እራሱን አቅሎ
ሲጠራኝ ሰማሁት የኔ ቢጤ ብሎ::
ያንተ ቢጤ ብሆን ሀብታም ባለዝና
ምን ያዘረጋኛል እጄን ለልመና?

የለጋሹ ቢጤ

Friday, June 26, 2015



ለፊደል እና ለትውፊት የሬድዮ ፕሮግራም የተገዙት መቅረፀ ድምፆች የውሀ ሽታ ሆነዋል

ለፊደልና ለትውፊት የሚያገለግል ኋላ ቀር መቅረፀ ድምፅ
የፊደል እና የትውፊት የሬድዮ ፕሮግራም በድምሩ የሁለት ሰአት የአየር ሽፋን የያዘ ሲሆን በሶስት መቅረፀ ድምፆች ብቻ ሲሰራ ቆይቷል። 

መቀሌ ዩንቨርስቲ ለዚህ በጀት መድቦ ተጨማሪ መቅረፀ ድምፆች እንደተገዙ ከተነገረ ሰንበትበት ያለ ሲሆን እስካሁን ድረስ ግን የመቅረፀ ድምፆቹ ወሬ የውሀ ሽታ ሆኖ ሰንብቷል። 

የመቀሌ ዩንቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ትምህርት ክፍል ዲን የሆነው መምህር መብርሀቴን ይህን ችግር በተደጋጋሚ ለበላይ አካላት አሳውቆ ምንም አይነት መፍትሄ እስካሁን እንዳልተገኘ እና ከዛሬ ከነገ መቅረፀ ድምፆቹ እጃችን ይገባሉ በሚል ያልትጭብጠ የስፋ እየተጓዙ እንደሆነ ተናግሯል። 
 በማከልም “እስከ አርብ ግንቦት 21 2007 ዓ.ም አምስት መቅረፀ ድምፆች ይደርሱናል” ሲል የተለመደ የተስፋ ቃሉን አስቀምጧል። የመቀሌ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንትም ዶክተር ክንደያ ገ/ህይወትም በበኩላቸው “ይህ በማንኛውም የስራ ዘርፍ ሊያጋጥም የሚችል ችግር ስለሆነ ተማሪው በትእግስት ሊሰራ ይገባል። መቅረፀ ድምፆች ተገስተዋል። በቅርቡ እጃችው ይገባሉ” ሲሉ ያላቸውን እስተያየት ገልፀዋል።

Wednesday, June 24, 2015



"I would like to assure you that you are studying an excellent field if it is of your passion..."

online interview with Hailemelekot T. Birhan

(He works in the leading media consulting company; contributes to the weekly English newspaper, Fortune; he also travels to Canada and Turkey spearheading a delegation consists of Ethiopian investors ant the media) 

 Temesgen Shiferaw:-
From the perspective of press freedom, does online journalism has it's own rules or some other different laws? In other words, what is the press freedom for online journalism?

Hailemelekot:-
It's really an interesting point you raised.
Online journalism has its own rules and regulations which has to abide by in so many countries around the world. Yet, there is no such law that governs it here in Ethiopia. As to my understanding the essence of press freedom in online journalism is not different from that of traditional media. Yet, we have to wait for the laws to be promulgated here in Ethiopia.

Habtamu Abera:_
 Is research important for journalism students? Is research or documentary more crucial?

Hailemelekot:-
"Well, research is crucial for journalism. If you are a journalist you are always researching because you need to find out the fact and the truth. The same goes to documentary. If you are provided with a task to produce a documentary, still you need to do a research. Hope you will learn more about research in the times ahead."

Michelle Elias:-
What do you think ,Can bloggers would be journalist according to our ethics of journalism???

Hailemelekot:-
Well, bloggers can be journalists or not. The way they do their reporting matter. As you might be well aware, journalists try to tell the objective truth, report facts fairly, strives for balance and disclose bias.So,what matters here is whether bloggers do exercise these very components or not. Experience shows that some bloggers simply put opinions in their blogs and some strives for those ideals stated above. You also do need to bear in mind that a glut of journalists do have their own blogs.

In a nutshell, you can call those bloggers who are in line with journalistic ethics bloggers and the others not.


Riste Tsegaye:-
After the emergence of citizen journalism, Professional journalism become a dying profession. so what is your Advise to professional journalists to enhance the field???

Hailemelekot:-
 I wonder the mainstream media is dying due to citizen journalism. Both are working in their own way and no doubt the latter poses a challenge on the former. But I don't think it reaches on survival level. Just be loyal to the profession and keep all the ethics and professionalism if it needs to thrive in the future.

Wendifraw Tesisa
What will be the future of journalists and traditional media???

Hailemelekot:-
 In a broader sense, as to my understanding the future of journalists and the mainstream
 media will remain bright. They will keep on going provider of the main
 source of information. Yet, there is an insurmountable challenge the
 mainstream media faced from what recently dubbed " Citizen Journalism" or
 "Social Media".

  In this regard, it seems that this very social media broke the stories
  world wide preceding the mainstream media. So in the future, the lingering
  reality is " For whom the mainstream media break the stories"? Citizens are
  everywhere and they will tweet,post on Facebook etc. right away.
all, we can see and share experience with each other

Almaz Abebe:-
The traditional media is become dead by social media. So in your perspective what is the value of a journalist in this time?

Hailemelekot:-
It seems there is some sort of exaggeration on the remark that the mainstream media is dying due to social media. As to my knowledge, even if there is a challenge from the social media on the mainstream media, it doesn't lead to survival. So, the value of a journalist will pursue on as it is

Gedam Gebru:-
What will be the future of professional journalists while there are many citizen journalists?

Hailemelekot:-
There are challenges from citizen journalism on the mainstream media. But, I don't see the future of mainstream media that much gloomy. It will keep on playing a crucial role. Somewhat the missions of the two differ as well

Bezawit Teferi:-
What kind of ability journalists must have in social media to get the attention of audience?”

Hailemelekot:-
Well, journalists must have all the professional talent possibly what you have learned in your class including the ethics. So this also works while you are working in social media as well
Mr. Hailemelekot T. Birhanu


Endale Elias:-
   For what purpose you use online media? Why you chose to use it?

Hailemelekot:-
I use online media mainly to get information as to my areas of interest. I choose to use online media as it provides up-to-date information instantly

Meseret G/Medhi:-
Online media can be expand from time to time so, what do you think
about our feature traditional media?

Hailemelekot:-
The future of traditional media in Ethiopia will not be different from the online media. There are several factors for this including internet connectivity and access to computer. You can guess the penetration rate of internet in Ethiopia. Thus, there is a huge potential both for the mainstream media and online media to thrive in Ethiopia in the future

Mesfin Kassahun:-
How do  you describe the impact of new media on journalism?

Hailemelekot:-
The social media (new media) seems broke the stories preceding the mainstream media nowadays. So its impact is that more people may get up-to-date information from the social media than the mainstream media. You might guess what is going to happen if it pursues like this. More and more people might give attention to the social media than the mainstream media.

Behailu Gezahegn:-
What do you think about the role of Ethiopian broadcast media on political system of Ethiopia?

Hailemelekot:-
As any country, the broadcast media plays an insurmountable role in influencing and guiding the political atmosphere in Ethiopia. What may differ is that the role of the media in stirring the politics in Ethiopia is not that much of other developed nations.Bear in mind that our system has its own limitations.

Selam Wuletaw:-
What do you think of the use of learning online journalism?

Hailemelekot:-
Now a days there is an increase in the number of bloggers, do you think this can affect the journalist work? By the way I want to admire you. I expect your answer. Thank you.


 Well, at the current digital age you should learn online journalism as it will become the main source of information to people along with the mainstream media. Journalists in the mainstream media should cope-up with the overall changes quickly and adapt themselves. Doing this, they can minimize the effect of online journalism. So it may affect the audience of the mainstream media but journalists can be part of it and do their jobs respecting the professionalism and ethics

Semhal Mekonnen:-
To be a journalist you have to be advocator of the government. And how can i be a neutral and objective journalist in this situation?

Hailemelekot:-
Well, it depends on the environment you are working on. If you are working on government media, you may be obliged to have a pro-government tone. Yet, what you need to understand is that, even if you are working on  a private media, as the professional ethics says so, you need to dig out the truth and the fact. You don't need to be biased. Yet, as a private media, you may have some thoughts which you stand for. So, as long as you are aware of the ideals of journalism, there are private media as well. So you can join there and grow your career

Hanna Kiflu:-
What's your idea about the impact of social media on the profession of journalism?

Hailemelekot:-
The social media seems broke the stories preceding the mainstream media nowadays. So its impact is that more people may get up-to-date information from the social media than the mainstream media. You might guess what is going to happen if it pursues like this. More and more people might give attention to the social media than the mainstream media

Tsion Hailu:-
 What do you think about to days Freedom of Press and Freedom of Expression in Ethiopia?

Hailemelekot:-
To be honest with you, the issue of freedom of press and freedom of expression is quite a delicate matter in Ethiopia. It seems you are also very much aware of that and tried to change the angle of your question from what you have said specifically about Ethiopian to a general sense latter. It doesn't mater.We can talk about the issue in Ethiopia in a precise way.

Freedom of press and expression is a constitutionally guaranteed right in Ethiopia as per Article 29 of the FDRE Constitution as well as subsequent proclamation of the Freedom of the Mass media and Access to Information,590/2008. In fact the laws are there, but serious irregularities are observed in the implementation. What you have to bear in mind that, developing professionalism is very crucial while working as a journalist. This gives you the credibility and doesn't give any room of error for those who might be critical of it. Yet, even if the framework is there, some one should not feel everything is smooth as of the developed nations.

Andualem Semachew:-
How do  you think about the progress of online journalism in Ethiopia ??

Hailemelekot:-
Online journalism in Ethiopia is at early stage. It is very much infantile. As you know one needs to have internet connection and a computer to engage in online journalism. I think you can make an educated guess on how many people do have internet connection and access to computers in Ethiopia. It heavily relies on that. In fact nowadays people can have internet access from their phones but that is still limited. Just think the progress of online journalism in this context.

Elias Shume:-
Nowadays News and Information is written
and published by any ordinary person out of his/ her profession
in social media like Facebook ,twitter and any information  news is
reached for millions with in a second.

What do you think about this issue as professional , what would be the
role of a journalist for future?

Hailemelekot:-
The emergence of social media and its ability to garner more and more people to it is a plus as a way of alternative source of information. But you need to bear in mind that the social media is more of people's opinion and not exactly the same with the mainstream media. The mainstream media is looking for facts and truth.

But journalists will keep on doing their professional work at least in the near future with all the components of its professionalism and ethics.

Melat Mirco:-
What do u think the effect of  social media is on the work of journalists?

Hailemelekot:-
The question you raised is one of the lingering issues circling the journalism profession.

The social media seems broke the stories preceding the mainstream media nowadays. So its impact is that more people may get up-to-date information from the social media than the mainstream media. You might guess what is going to happen if it pursues like this. More and more people might give attention to the social media than the mainstream media. But but this is not an insurmountable problem for the mainstream media. Still there is ample room to work on it.
Best,
Haile

Nahom Tadesse:-
Do you think journalism is a field that has to be given at University level? More specifically, from the perspective of citizen journalism, should this field be given by degree?

Hailemelekot:-
I would like to assure you that you are studying an excellent field if it is of your passion. You don't need to worry about the challenge of citizen journalism that much. It's undeniable that it poses a challenge but don't consider it as a threat and discourage you.

Sure, journalism will keep on one of the fields to be provided in Universities and follow your ambitions.

Frehiwot:-
how are  using the on line media? i want to share some of your information about that

Hailemelekot:-
I use online media mainly to get information as to my areas of interest. I choose to use online media as it provides up-to-date information instantly

Tsion Kibru:-
As you are working on media consulting company and also experienced both the traditional and the new media in the country,how far do you think the development of citizen journalism in the country is becoming a challenge for the traditional media in revising its content?

Hailemelekot:-
Citizen journalism is becoming a challenge to the mainstream media around the globe. Yet, in the context of Ethiopia, you don't need to consider it as a challenge yet. This is due to the fact that both the mainstream media and the social media are at an early stage of development. There is still a huge potential on both sides to work on it.

Bisrat Kiday:-
Now a days every body becomes a journalist so what is the use of professional journalist?

Hailemelekot:-
There are challenges from citizen journalism on the mainstream media. But, I don't see the future of mainstream media that much gloomy. It will keep on playing a crucial role. Somewhat the missions of the two differ as well.

Haimanot Wendimu:-
 in online journalism we can advert any good's and service so how to get payment?

Hailemelekot:-

In Ethiopia, you make an agreement in advance including the payment before the ad is posted physically going to office or in some other mechanisms. You can collect the money in this manner. Yet, in most countries, electronic payment methods such as visa card and master card is possible
 
Abel Dejene:-
What do you think about the future journalism?

Hailemelekot:-

Be sure that the future of journalism is very much bright. You joined a very good, dynamic and ever-growing profession. It's quite interesting to to live in a changing environment while reporting it at the same time. In fact there are lots of challenges but not insurmountable.



That's it. I would like to thanks both our instructor to give us the chance to contact such a wisely experienced person and Mr. Hailemelekot himself too, for his cooperation by answering all the questions. And thirdly all my classmates for your strong participation. We will be in touch with another interview next time.