(የሰው
ልጆችን ባህሪና እጣ ከሚናገሩት የወራት ኮከቦች በግንቦት ወር በተወለደ ሰው ኮከብ ላይ የተመሰረተ ግጥም)
ኮከብሽ
ሲፈታ
ግንቦት
ነው ውልደትሽ በግለቱ ፀሀይ
ሀሩር
ሲገባደድ ለዝናብ ሩብ ጉዳይ::
እና
በዚህ ወር ላይ ወደምድር የመጣ
ውዝግብግብ
ነው እድሉ አከራካሪ እጣ
ግትር
ነው ልቦናው ጨካኝ በባህሪ
እማ
እንዲ ነሽ እንዴ ለሰውም አትራሪ?
ደሞ
ዝቅ ብሎ ኮከብሽ ሲነበብ
ግሩም
አይምሮ አለው የሰላ አስተሳሰብ::
ይህን
ማን ይክዳል?
እጅሽ
ካላጠረ የሙት ልጅ ካበላ
ከወዴት
ሊመጣ ካንቺ በላይ የሰላ?
በፈጠረሽ
እማ
ይህን
ስል አይምሮ የአብራክሽ ክፋይ ለምነው ያልወረሰው?
ወይ
አንቺ ራስ ወዳድ ወይም ደሞ ልጅሽ ማሰብ ያቃታው ነው ::
ትዝ
ይልሻል እማ በሳት ዳር ጨዋታ
የእግሮችሽን
ቅጥነት የጠየኩሽ ለታ?
አንቺማ
ዋሸሺኝ እንዳይቀንስ ፍቅሬ
የእሳት
ልጅ እሳት ነው ደረስኩበት ዛሬ::
እጣ
ክፍሉ ሆኖ ግንቦት የወለደው
ቤት
መዋል ይጠላል እግረኛ ተጓዥ ነው::
መጓዝ
አይጠላም መገስገስ ደግ ነው
ግን
እማ ያንቺን ጉዞ ዳና ስ ያረገው
ወደላይ
ነው እንዴ ልቴጅ የፈጠረሽ?
የመሬት
ስበት ነው እዚያው የመለሰሽ?
አንቺ
ብትሸሽጊኝ ሀቅኮ ንጋት ናት አትቀር ተደብቃ
ጉደኛ
ኮከብሽ መች በዚህ ሊያበቃ…
በዚህ
ወር ዓለምን የተቀላቀለ
ብዙ
ልጅ የለውም የሚል ሀረግ አለ::
እዚ
ላይ እውነት አለው ካላደለሽ ባርኮ
ካብራክ
የወጣ ሁሉ ልጅ አይደለምኮ::
ስል
ካማጠ ሆድሽ መጋዝ ከፀነሰ
ባቢሎን
ካረገዝሽ ሳይቋጭ የፈረሰ
ማህፀንሽ
ከከዳ ጭድ ከበቀለበት
መወለድ
ቋንቋ ነው ፊደል ነው ልጅነት::
እማኮ
ትንፋሽሽ
ቁርጥ
ቁርጥ ይላል ብዬ ስጠይቅሽ
ደበቅሽኝ
ደዌሽን አልችል አለ አንጀትሽ::
እውነቱ
ግን እማ…
የዚህ
ወር ዘለላ ገና ከጥንስሱ
ትንሽ
ደከም ይላል አተነፋፈሱ::
ሳንባሽም
ደከመ? እና ምን ቀርቶሻል?
ትንባሆ ገሎሻል ወይ ድመት ወልደሻል
ምንድነው
የደበቅሽኝ? እስትንፋስ ቀልድ ነው?
አዳምኮ
ያኔ ህይወቱን የዘራው በጌታ ትንፋሽ ነው::
ደሞ
ዝቅ ስንል ኮከብሽ እንዲ ይላል
ግንቦት
የሚወለድ ጆሮውንና አንገቱን ብዙ ግዜ ያመዋል::
እዚህ
ላይ ፉርሽ ነው ቀባጣሪ ኮከብ!
ለሀዘን
ፅዋ አርጎሽ ለመከፋት ሰበብ
አንድ
ለናቱ ሆነሽ በጤነኞች መሀል
ምን
የቀረሽ አለ ያልታመምሽው አካል?
ቆይ
እንጂ ረጋ በይ ስሚ ኮከብሽን
ሩቅ
ማሰብ ሩቅ ማለም ቶጃለሽ ያለሽን
በዚ
እንኳ አትታሚም አንደራደርም
ያንቺን
የሩብ ግማሽ ዘንዶም አያልምም::
ግን
እማ ንገሪኝ
ሲመሽ
አስተዳድሮሽ ሲነጋ ሚከንፈው
የተካነ
ጠበብት ሎሬት የማይፅፈው
ብርሀን
የሚፈራው ያ ጭሱ ራእይሽ
ለምፃት
ነው እንዴ የሚፈታው ህልምሽ?
ጉዱን
ለቀባሪው ማርዳት ባይሆንብኝ
ልንገርሽማ
እማ ምን እንዳነበብኩኝ
ካስራ
ሁለት ወር ነጥቆ ግንቦት የወለደው
ስነ-ፅሁፍ
ወዳድ ጥበብ አድናቂ ነው::
ይሄማ
ግልፅ ነው ጥበብሽ መች ታጣ
ድሮ
አንቺ የሌለሽን 'ኔ ከየት ላመጣ?
ግን
እማ እኔ ያልገባኝ…
መቶ
ሀያሲ ታቅፎ ሺ ሎሬት ደርድሮ
ከእልፍኝ
በማይወጣ በጭብጨባ ታስሮ
የግዜ
እርከን መሆን የጠቢብ ጣራ ነው?
ምን
ካንቺ ባላውቅም ጥበብ ማለትኮ ሀገር ሲቀይር ነው::
ግርምቴን
ልቀጥል? እማ አታዝኚብኝም?
ብርቅኮ
ሆኖብኝ ነው! ጉደኛ ኮከቤ ምን አለ አትይኝም?
የዚህ
ወር አርበኛ ከሌላ ሚለየው
ባካልም
ባይምሮም የተዋበ ሰው ነው::
ይገርማል
አይደለ? ይህን እንኳ አታቂም
ውበት
በባህሪው ለተመልካች እንጂ ለራስኮ አይታይም::
ለምን
ይመስልሻል ያ ሁሉ ተጋዳይ
ጦር
ጎራዴ ይዞ የመጣው ባንቺ ላይ?
ጀግና
የተጣላብሽ ቆንጆ ነሽ እመኚኝ
ይልቅ
እሱን ትተሽ ምን ገረመህ በይኝ
እንዴት
የተዋበ አስቀያሚ ይወልዳል?
ከተሳለ
አይምሮስ ጭፍጋግ አስተሳሰብ እንዴት ይፈጠራል?
ምን
ዥንጉርጉር ቢሆን ሺ ቢያደላ የእናት ሆድ
ተባርኮ
ፀንሶ ያለም መርገም ይውለድ?
አዎ
አንቺማ ሳቂ…ደሀውን ይግረመኝ
ወዳጄ
ኮከብሽ ጠንካራ ፍላጎት እንዳለሽ ነገረኝ::
አሁን
እኔ ልሳቅ…
እማ
አሁን ፍላጎት ምን ያደርግልሻል?
ምሰሶ
ያላርማታ ብቻውን ሲፀና የት ሀገር አይተሻል?
ለፍላጎትማ
አዳምስ ሲፈጠር
የጌታውን
ወንበር ተመኝቶ አልነበር?
እስኪ
ብቻ ተይው…
ይህ
ሁሉ በባህሪሽ የባህር ውሀ ነው ቢቀዝፉት አይደርቅም
እንኳን
በኔ አንደበት በራስሽ አያልቅም::
እንዲ
እንዳስገረምኩሽ አልቀርም አትስጊ ብዙ አወጋሻለው
ደሞ
ሌላ ጊዜ የልጅሽን ኮከብ የኔን ነግርሻለው::
ናሆም ታደሰ
No comments:
Post a Comment